ቆስቋሽና አቆሳቋሽ

‹‹ቆስቋሽና አቆሳቋሽ››

‹‹ይ’ች ሀገር እንደዚህ፣ የምትታመሰው፤

ማነው ማማሻውን፣ የሚቆሰቁሰው?››

ብለህ የጠየቅኸኝ…

ተከሳሽ ፈልጌ፣ የጥንት ማመካኛ፤

‹‹ሰይጣን ነው›› ልበልህ? ያንን መከረኛ?

.

አትሸወድ ጓዴ…

ከመካከላችን፣ ሥጋ የለበሰ፣ ክፉ ሰይጣን አለ፤

በመንፈስ፣ በግብር፣

ያንን የጥንት ጠላት፣ እ ር ሱ ን የመሰለ።

‹‹ይህ ያልኸውስ ማነው?››

ብለህ እየጠየቅህ፣ ልቤን አታድርቀው፤

አቆሳቋሹ ነው፣ ቆስቋሹን የሚያውቀው።

.

ያው ላ’ቆሳቋሹ፣

ቆስቋሹን ማጋለጥ፣ ቢመርም ባይመርም፤

ይዘገያል እንጅ፣

የቆሰቆሰው ሳት፣ ዞሮ ሲያቃጥለው፣ መናዘዙ አይቀርም፡፡

—›

መላኩ አላምረው

Facebook Comments

Post Author: መላኩ አላምረው

መላኩ አላምረው
Melaku Alamrew