ተቃርኖ – የሺሀሳብ አበራ

ተቃርኖ – የሺሀሳብ አበራ

ለህዳሴው ግድብ አማራ ከ 1.2 ቢሊየን ብር በላይ በማዋጣት ከሃገሪቱ ቀዳሚ ነበር፡፡ነገር ግን ከ 30% ሳያልፍ 64% ደርሷል ተብሎ ብሩ ተዘረፈ፡፡ በህዳሴው ግድብ የሚሰሩ አማራዎችም ይታሰሩ እና ይፈናቀሉም ነበር፡፡

….

የሌለ ለመፍጠር 1.2 ቢሊየን ብር ያዋጣው አማራ ጣናም ሆነ ላሊበላ የነበሩት ሲጠፉ 50 ሚሊየን ገና አላዋጣም፡፡ መቼም ሃገሪቱ ጣና ሆነ ላሊበላ ይመለከተኛል እንደማትል ይታወቃል፡፡

አማራ የራሱ ባንክ ስሌለው ብቸኛ መቆጠቢያው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነው፡፡ ባንኩ ኢትዮጵያ የሚል ስያሜ ስላለው አማራ ይወደዋል፡፡ ስለሚወደው ጎንደር፣ባህርዳር እና ደሴ የሃገሪቱን ከፍተኛ ትርፍ ይገኝባቸዋል፡፡ ንግድ ባንክ ከፍተኛ ገንዘብ ከአማራ እያገኘ ዝቅተኛ ብድር ለአማራ ይሰጣል ፡፡ይሄን ያነሱ የንግድ ባንክ ሰራተኞችም የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ እየደረሳቸው ነው፡፡

መለስ ሲሞት በአማራ ምድር ተቋማት መለስ መታሰቢያ፣መለስ ፓርክ፣ታላቁ መለስ… እየተባሉ ተሰየሙ ፡፡ ጤና ጣቢያዎች ግንቦት 20 ተባሉ፡፡የግንቦት 20 ስያሜ ከየትኛውም የሃገሪቱ ክፍል አማራ ላይ ይበዛል፡፡ከየትኛውም የሃገሪቱ ክፍል ግንቦት 20 የጎዳው ግን አማራን ነው፡፡አማራ በጎዳው ነገር እንዴት ይሰየማል? መልሱ ራስን ያለመሆን ጣጣ ነው፡፡

….

ጠሚዶ አብይ ወደ ስልጣን ሲመጡ ከፍተኛ ፖስተሮች የተቸረቸሩት አማራ ላይ ነው፡፡ጠቅላዮ በከፍተኛ ሁኔታ ተቀባይነት ስላገኙ ትምህርትቤቶች ሁሉ አብይ ተብለው ተሰይመዋል፡፡የጠሚዶ አብይ ምስል በየተሽከርካሪዎች፣በየአደባባዮ በብዛት ተለጥፏል፡፡ይህ ጠቅላዮ ከተወለዱበት አጋሮም የለም፡፡ ከአጋሮ በላይ ወልዲያ ወይም ደብረብርሃን ስለ ጠሚዶ አብይ ተደስታለች፡፡

ነገር ግን የአብይ አስተዳድር አንድም የአማራ ጥያቄ አልመለሰም፡፡ይባስ ብሎም በአዲስ አበባ የገፍ እስሩ በርትቷል፡፡” ፊንፊኔን ማስመለስ” የሚል ማህበር የከንቲባ ታከለ ኡማ ደጋፊዎች ሲያቋቁሙ፣አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ናት የሚል ማህበር ለማቋቋም ያሰቡት ጠበቆች ወደ ዘብጥያ ወርደዋል፡፡

50% ሴት ሚኒስተር ተመረጠ፡፡ሃገሪቱ ከአረብ ጋር ተወዳጀች፡፡ጠሚው በዓለም የመጀመሪያው ዲሞክራሲያዊ መሪ ነው እያለ ፕሮፖጋንዳ እየጠጣ አማራ ፍትህ ይራባል፡፡

….

እነ ጌታቸው አሰፋ የኢህአዴግ አስፈፃሚ ሆነው በክብር ሲሾሙ፣የዋህ አዲስ አበቤ በግፍ ይታሰራል፡፡

በእርግጥ ፍትህ ማደሪያው ከአሸናፊነት ብቻ ነው፡፡ፍትህ በፍትህ አይመጣም፡፡እውነት በአሸናፊዎች እጅ ብቻ ናት፡፡እውነት በራሷ ነፃ አታወጣም፡፡ ነፃ ለመውጣት ራስን መሆን ፣በራስ መሆን ውስጥ ጥቅምን ማስላት ያስፈልጋል፡፡በሰው ሰርግ እየዘፈኑ ብቻ መኖር ሩቅ አያስኬድም ፡፡

አማራ ይቅደም!!

Facebook Comments

Post Author: መላኩ አላምረው

መላኩ አላምረው
Melaku Alamrew