Smokind Danger

አስደንጋጭ ሲጋራ ነክ ሐቅ !

አስደንጋጭ ሲጋራ ነክ ሐቅ !
በዓለም በየቀኑ 26,000 ሰዎች ከትንባሆ (ሲጋራ) ጭስ ጋር በተያያዙ በሽታዎች ይሞታሉ። ከእነዚህ መካከል 6,000 የሚሆኑት በቀጥታ የማያጨሱና ሌሎች ሲያጨሱ በቅርበት በመኖራቸው ምክንያት የሚደርሳቸው ናቸው። በተለይም ሕፃናት ያለ ኃጢአታቸው እየሞቱ ነው።

በሀገራችን ከ7 ሚሊዮን በላይ አጫሾች አሉ። ይህ ቁጥር በቀጥታ የሚያጨሱትን ብቻ የሚገልጽ ሲሆን ምንም ዓይነት ጥንቃቄ የማይደረግባት ሀገር በማሆኗም በተዘዋዋሪ ጭሱ የሚደርሳቸው ሰዎች ቁጥር እንደሚበልጥ ይገመታል። ሰው በሚሰበሰብበት አካባቢ ማጨስን የሚከለክል አዋጅ እንደወጣ ቢነገርም ተግባራዊ አልሆነም።

አዋጅን ግን የማስፈጸም ግዴታው የማነው??? ማጨስ የሚፈቀድባቸውና የማይፈቀድባቸው ቦታዎች ተለይተዋል??? የማይፈጸም ሕግ መኖሩ ምን ይጠቅማል ?

ለማንኛው የትንባሆ ገዳይነት በቀን 26 ሺ ሰዎች ይሞታሉ ሲባል ከእነዚህ ውስጥ 6 ሺዎቹ በተዘዋዋሪ የደረሳቸው መሆናቸውን ተገንዝበን ራሳችንን ከናጨስ ብቻ ሳይሆን ከሚያጨሱም ማራቅ ግድ ይላል። ጉዳዩ የሕይወት ጉዳይ ነው። በተለይ ሕፃናትን እንታደጋቸው።

—›

ይህ ጉዳይ ያሳሰበው የኢትዮጵያ የምግብ፣ የመድኃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን የሚከተለውን መልእክት አስተላልፏል፡-

‹‹የዓለም አቀፍ የጤና ድርጅት መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በሲጋራ ምክንያት ያለእድሜያቸው የሚሞቱት ሰዎች ቁጥር ከሰባት ሚሊዮን ያልፋል፡፡ ከነዚህ መካከል ወደ 1 ሚሊዮን የሚጠጉት ቀጥታ አጫሽ ሳይሆኑ ሲጋራ በቀጥታ የማያጨሱ በህዝብ መሰብሰቢያ እና መሰል ቦታዎች ለሲጋራ ጪስ የሚጋለጡ (passive smokers) ናቸው፡፡ ይህ ቁጥር በኤች አይ ቪ፣ በወባ፣ በቲቢ እና በትራፊክ አደጋ ህይወታቸውን ከሚያጡ ሰዎች ቁጥር ድምር ይበልጣል፡፡ በአገራችን ኢትዮጵያ የችግሩ አሳሳቢነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው፡፡ ጠንካራ የትንባሆ ቁጥጥር ህግ ያላቸው ሀገሮች ትንባሆ የሚያደርሰውን የጤና፣ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳት መቀነስ ችለዋል፡፡ይህ እንዲሆን ደግሞ ሀገራችን ጠንካራ የትንባሆ ቁጥጥር ሕግ ያስፈልጋታል፡፡
የሲጋራ ጭስ ይገላል!
ዜጎች በትንባሆ ጭስ የአልጋ ቁራኛ ከመሆን የሚታደጋቸው ህግ ይፈልጋሉ!!››

Facebook Comments

Post Author: መላኩ አላምረው

መላኩ አላምረው
Melaku Alamrew