አዲስ አበባ ወይስ ጓንታናሞ…

አዲስ አበባ ወይስ ጓንታናሞ…

* ጠላት ሀገር እንኳን በዚህ መልኩ አይዘረፍም! ~ ጠቅላይ አቃቢ ህግ ብርሃኑ ጸጋዬ

* አዲስ አበባ ውስጥ 7 ግፍ የሚፈፀምባቸው ድብቅ እስር ቤቶች ተገኙ

* የሰኔ 16ቱ የአዲስ አበባው የቦምብ ጥቃት የብሔራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎት የቀድሞ ኃላፊ የተመራ ነው

***

« በአዲስ አበባ ዜጎች ከሰባት ወደማያንሱ ስውር ማሰቃያ ስፍራዎች ‘በአምቡላንስ እየተጓጓዙ!’ ኢ- ሰብአዊ ድርጊት ይፈጸምባቸው ነበር »

በእነዚህ እስር ቤቶች ዉስጥ

– ሴቶች ይደፈራሉ

– ወንዶች ግብረሰዶም ይፈፀምባቸዋል

– ወንዶች ብልታቸዉ ላይ ሀይላንድ ይንጠለጠልባቸዋል

– አይናቸውን ታስረው በጫካ ይጣላሉ

***

ፖሊስ ጣቢያ፣ ማረሚያቤት እና ስውር እስር ቤቶች ውስጥ የነበሩ ተጠርጣሪዎችን በአሌክትሪክ ሾክ ማድረግ፣ ብልትን በፒንሳ መሳብ፣ ዛፍ ላይ ሰቅሎ ለረጅም ጊዜ ማቆየት፣ ጫካ ውስጥ እርቃንን ማሳደር፣ ጥፍር መንቀል፣ በብልት ላይ ውሃ ማንጠልጠል፣ አይናቸው ከታሰረ በኋላ ከከተማ አውጠቶ ጫካ ውስጥ መጣል፣ አልፎ አልፎ ከአውሬ ጋር በማሰር ማሰቃየት ሲደረግ ነበር

***

የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽንን በተመለከተ፦

ከ2004 እስከ 2010 ድረስ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን 37 ቢሊየን ብር የውጭ ግዢ ፈፅሟል።

እነዚህ ግዢዎች ዓለም አቀፍ ጨረታ ሳይፈፀምባቸው የተከናወኑ ናቸው።

ግዢዎቹ በጥቅም በተሳሰሩ ግለሰቦችና ተቋማት መካከል የተከናወነ ነው።

***

“የሰኔ 16 ቱ የቦምብ ጥቃት የተቀናበረው በብሔራዊ መረጃና ደህንነት ቢሮ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኦሮሞ ስለሆኑ በኦሮሞ ቢገደሉ ተብሎ ነው በሙከራው ኦሮሞዎች እንዲሳተፉ የተደረገው።”

***

ሜቴክ ከ2004-10 ዓ.ም ከ 37 ቢሊዬን (2.5 ቢሊዬን ዶላር) የውጭ ግዢ ያለጨረታ ከውኗል።

የሃገር ውስጥ ግዢ ሙሉ ለሙሉ ያለጨረታ ተከናውኗል።

የሀገር ውስጥ ግዢም በግልፅ ጨረታ መፈፀም ሲገባው እስካሁን በዚህ መልኩ የተፈፀመ የለም። ከኮርፓሬሽኑ አመራሮች ጋር የዝምድናና የጥቅም ትስስር ካላቸው ሰዎች በብዙ እጥፍ በተጋነነ ዋጋ ይገዛ ነበር። ከአንድ ድርጅት 21 ጊዜ፣ ከሌላው ደግሞ 15 ጊዜ ግጭ ተፈፅሟል። ከአንድ ድርጅት በአንድ ጊዜ ብቻ የ2015 ሚሊዮን ብር ግዢ ያለጨረታ ተፈፅሟል።

***

ከተቋሙ ተልዕኮ ውጪ የተፈፀሙ ግዥዎችም አሉ። ከዚህም ውስጥ የመርከብ ግዢ ይገኝበታል። በማይመለከተውም ስራ ገብቶ ወደ ንግድ ስራ አስገብቷቸዋል

***

በሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀል 36 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል

***

በአጠቃላይ እስካሁን በቁጥጥር ስር የዋሉ የሜቴክና ደህንነት አመራሮች ቁጥር 63 ሲሆን እስካሁንም ያልተያዙ በአገር ውስጥና ከአገር ውጭ የተደበቁ አሉ።

***

የሰኔ 16ቱ የአዲስ አበባው የቦምብ ጥቃት የብሔራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎት የቀድሞ ኃላፊ የተመራ ነው

***

የመረጃ ደህንነት ኃላፊው ማን እንደሆኑ እያወቃችሁ አታድርቁኝ ።

***

ወንጀለኛ የማንም ብሔር ተወካይ አይደለም፡፡

***

በሙስና 27 ሰዎች፣ በሰብዓዊ መብት ጥሰት ደግሞ 36 ሰዎች በአጠቃላይ ከ 63 በላይ ተጠርጣሪዎች መያዛቸውን ነው በመግለጫው የተመለከተው፡፡

~ ( ከአቃቤ ሕግ መግለጫ

Facebook Comments

Post Author: መላኩ አላምረው

መላኩ አላምረው
Melaku Alamrew