No Gun

ከ500መቶ በላይ ሽጉጦች፣ 3 መትረየስ ፣ 100ሺ የሚጠጉ የተለያዩ ጥይቶች እና ከ30 በላይ ክላሽ ተይዟል

በህገ ወጥ የገንዘብና የጦር መሳሪያ ዝውውሩ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር የዋሉት ተጠርጣሪዎች ብዛት 18 ደረሰ።

ከአምስት መቶ በላይ ሽጉጦች፣ ሶስት መትረየስ ፣ መቶሺ የሚጠጉ የተለያዩ ጥይቶች እና ከ30 በላይ ክላሽ ተይዟል

ሰሞኑን በብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ በፌደራል ፖሊስ እና በኦሮሚያ ፖሊስ ትብብር የተያዙ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች መያዛቸውን ተከትሎዝውውሩ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር የዋሉት ተጠርጣሪዎች ብዛት 18 ደረሰ።

የህገ-ወጥ የገንዘብና የጦር መሣሪያ ዝውውርን ለመከላከል እየተካሄደ ያለው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘይኑ ጀማል ለኢቲቪ የገለፁ ሲሆን
አስካሁን በአዲስ አበባ 234 ሽጉጥ 17 ሺህ የሽጉጥ ጥይት፣ በጋምቤላ 2 መትረየስ 32 ክላሽ፣ በምእራብ አርማጭሆ 298 ሽጉጥ፣ በሰሜን ሸዋ ሸኖ 1መትረየስ 20 ሽጉጥ፣

በአዲስ አበባ ደግሞ ኮልፌቀራኒዮ፣ ጉለሌ እና የተለያዩ አከባቢዎች ብዛት ያለው የጦር መሳሪያ እና 80 ሺ የሚጠጉ የክላሽንኮቭ እና የሽጉጥ ጥይቶች መያዛቸውን ተናግረዋል፡፡
መሳሪያዎቹ ከቱርክ በሱዳን እና በጅቡቲ አድርገው ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የተናገሩት ኮሚሽነሩበቁጥጥር ሥር እየዋለ ያለው ገንዘብና የጦር መሣሪያ የሃገሪቱን ሠላምና ኢኮኖሚ ማናጋትን ታሣቢ ያደረገ ነው ብለዋልም

Source: ሸገር ታይምስ

Facebook Comments

Post Author: መላኩ አላምረው

መላኩ አላምረው
Melaku Alamrew