(ዝብዘባ) – ኑርዬ አያሌው[ሉሲ]

ወጪ ወራጁን ለመመልከት ያመቸኝ ዘንድ መንገዱ ዳር ባለች አንድ ካፌ ቁጭ ብያለሁ።ጭብጨባዬን ያደመጠች የካፌው ታዛዥ ከተፍ አለች። “ምን ልታዘዝ..?” አለች ቀጠለችና ለስለስ ባለ አንጀት ጎትት ድምፅ ተጎናብሳ…ተቅለስልሳ። ማኪያቶ እንድታመጣልኝ ቀጭን ትዕዛዝ ሰጠኹዋት።

ግን..! እንደ’ኔ ላለ ሰው ከአስተናጋጅ በቀር ሌላ ከትህትና ጋር በአክብሮት ሊታዘዘው የሚችል አንድም ሰው ይኖራል ብዬ አላስብም።ምክንያቱም የለም..! ።ሌላው ቢቀር ታላቅ እና ታናሽ ይሉት የእድሜ ምድብ ገቢራዊነቱ ለልኳንዳ ቤት ብቻ እንደሚሰራ አሳምሬ አውቃለው። ስለዚህ ታናሼ ነኽና ሂድ ተላከኝ” ማለት አይነፋም..!። ታናሽን ታላቅህ ነኝ ማለት ትርፉ..! ቅሌታም መባል ነው።ለነገሩ ራስን እንደታላቅ ተመልክቶ ሌላውን ሰው ትንሽ የሚል ሰው ራሱ ትንሽ ነው። ሙት..!!

….

ታዛዤ የላኳትን ማኪያቶ ከፊቴ አስቀምጣ እንዳቀረቀረች ትሪዋን ይዛ ወደ መጣችበት ተመልሳ ሄደች።በሰላም ግቢ ብዬ በአይኔ ሸኘሁዋት። ያው ሂሳቧን አስባ ለመውሰድ ተመልሳ ስትመጣ በደንብ አይታለሁ ብዬ አስባለሁ።

ያመጣቺልኝን ማኪያቶ ፉት እያልኩኝ በማያገባኝ ጉዳይ ገብቼ በአስተናጋጇ እምረት እና እፍረት መገረም ጀመርኹኝ። ታዛዤን በአትኩሮት እንዳየኀት ከሆነ የምታምር አይናፋር ትመስለኛለች። ታዲህ እንዲህ እምታምር ሆና ሳለች ለምን ታፍራለች..? በሚል እሳቤ መልሱ የማይጠቅመኝን ጥያቄ ራሴን መጠየቅ ያዝኹ።ግን ለምን ታፍራለች..? ምናልባት እንደምታምር አታውቅ ይሆናል በሚል ምናልባታዊ መልስ ለጠያቂው ራሴ ራሴው መለስኩለት።

….

አንዳንዴ የተሰጠንን ነገር ካለማወቃችን የተነሳ እንዳልተሰጠን በመሆን የጎደለን ነገር እንዳለ እናስባለን።በዚህም የተነሳ በራስ መተማመናችን ከውስጣችን እንደ ጉም በኖ ሊሄድ ይችላል።

አንዳንዶች ደግሞ በተቃራኒው የተሰጣቸው ነገር ባይኖርም ያልተሰጣቸውን ነገር እንደተሰጣቸው አድርገው ያስባሉ።እናም በራስ የመተማመን ብርቱ መንፈስ ተላብሰው በጎደላቸው ነገር ከመሳቀቅ ይልቅ መመፃደቅ ይቀናቸዋል።መልከ ጥፉ አድርጎ ቢፈጥራቸው እንኳን ባለማማር ከማፈር ይልቅ መንቀባረር ያበዛሉ።ምክንያቱም የስነ ልቦናቸው ጥንካሬ በሌላቸው ነገር ከመኮሰስ በዘለለ መኮፈስ እንዲችሉ ያደርጋቸዋል።

…..

የያዝኩትን ማኪያቶ ጠጥቼ ብጨርስም፥ካፌውን ለቅቄ አልወጣሁም።ዞር ዞር እያለሁ ወጪውን እና ወራጁን መቃኘት ጀመርኹ።በዚህ መሃል ከወጪው ከወራጁ ተለይታ ትኩረቴን እና አይኔን ነጥቃኝ ቀጭ ቋ እያለች ተራራ የሚያህል ታኒዋን(መቀመጫዋን) ከኀላ እያስለፈለፈች አለፈች።እዛው ባለሁበት ሁኜ ቀአይኔ ተከተልኹዋት።

በከፍታው ኤቨረስት ተራራን የሚስተካከል መቀመጫዋን ከኅላዋ አስከትላ ስትሄድ ተመልክቼ በተወደደ ስጋ ይሄን ያህል የስጋ ክምችት እሷ ላይ ማየቴ ትኩረቴን ሳይስብ አልቀረም።ከመቀመጫዋ ኅላ በሃሳቤ ተቀምጬ ጥቂት ርምጃ ሸኝት እንዳረግኅት “ሰው ምን ይለኝ..!” የሚሉት ይሉኝታ አዕምሮዬ ውስጥ ብልጭ አለብኝና ከሽኝቴ ተመለስኹኝ።ከሽኝቴ እንደተመለስኹኝ ከፊት ለፊቴ ራቅ ብሎ የተቀመጠው ነጭ እና ጥቁር ፀጉር ያለው ሰው እስተቤቷ ይሸኛት ኖሯል ለኬ..! በጣም ተናደድኩኝ…

ሰው ምን ይለኛል..? ብዬ ግማሽ መንገድ ሸኝቻት መመለሴ ቆጨኝ።እኔ ምለው..! ከሴቷ የሰራ አካላት መሃል ይሄን ሸንጥ ዳሌ እና ቂጥ የሚሉት ነገር እኛ ወንዶች ብረት እንደሆንን ሁሉ(መንጌ ስታይል) እንደማግኔት የሚስበን ለምን እንደሆነ አይገባኝም። ምናባት..! ህይዋን ከግራ ጎናችን እንደተሰራቺው መቀመጫዋም የተሰራው ከወንዶች አይን ይሆናል ብሎ መጠጠር ደግ ባይሆንም አይከፋም። ጠር..ጥርርርርርርርር !!

.

(ሰናይ ቀን ይሁንላችሁ)

ኑርዬ አያሌው[ሉሲ]

Facebook Comments

Post Author: መላኩ አላምረው

መላኩ አላምረው
Melaku Alamrew