የሕይወት ምንጭ አለ

መኖርህን ማይወድ…

ሸክም ሲያበዛብህ፣ ነፍስህን ሊቀጣ፤

ከሸክምህ የሚልቅ…

ጽናት በመላበስ፣ ፈንቅለኸው ውጣ!

.

ተስፋ ለማይቆርጥ…

ማስተዋል ለቸረው፣ ጥበብ ለታደለ፤

ለቀብሩ ብለው…

ከሚጭኑት ሸክም፣ የሕይወት ምንጭ አለ።

ዳግም የሚወልድ….

ከሞት የበረታ………… ከኃይላት ያየለ !!!

Facebook Comments

Post Author: መላኩ አላምረው

መላኩ አላምረው
Melaku Alamrew