AU head quarter Design by Hailesilase

የአባቶችን ራእይ ማስፈፀምም ትልቅነት ነው! አባት ወቃሽ ትውልድ ነካሽ መሆን ያሳፍራል፡፡

ይህ አዲሱ “የአፍሪካ ኅብረት አዳራሽ” አይደለምን?
ለካንስ የሕንፃው “ዲዛይን” ቀድሞ የተሠራ ኖሯል።
(እርግጥ ሸገርም በምኒልክና ጣይቱ ነው ዲዛይኗ የተሠራው፡፡)
የታላቆቹ ራእይ እንኳንም እውን ሆነላቸው።
የአባቶችን ራእይ ማስፈፀምም ትልቅነት ነው!
ግና አባት ወቃሽ ትውልድ ነካሽ መሆን ያሳፍራል፡፡
እነዚህ የዘመን ተሻጋሪ ራእይ ባለቤት የሆኑ ነገሥታት ሲመሰገኑ የሚነስረው ትውልድ ማየት ይገርማል፡፡
በአጠቃላይ የአባቶቹን ታላላቅ ራእይ ከማስፈጸም ይልቅ በጎ ነገራቸውን ላለመስማትና በርካሽ ፖለቲከኞች የተተረከለትን የጥላቻ ስብከት ሳያላምጥ ውጦ ስድብን ብቻ የሚተፋ ትውልድን ማየት የመጣንበት ብቻ ሳይሆን የምንሄድበት መንገድም እጅግ አስቸጋሪ እንደሚሆን ማሳያ ነው፡፡
ሀገር የምትገነባው በአንድ ወቅት ግርግር ሳይሆን በዘመናት የትውልድ ቅብብሎሽ ነው፡፡ ያለፈውን መሠረት ሳናጸና ለአዲስ ቤት ግንባታ መሮጥ ካሰቡት ሳይደርሱ ለመውደቅ ነው፡፡
ላለፈው ባናመሰግን እንኳን ዝምታን መምረጥም ብልህነት ነው፡፡ ለአብሮነት ሲባል፣ ለአንድነት ሲባል ዝምታም ጥሩ ነው፡፡ ነገር ግን… ከመሳደብ ሳንቦዝን እንዴት ያለ አንድነት ልናመጣ ይሆን? የአንዱን ሕዝብ ጀግኖች ሳናከበር ከዚህ ሕዝብ ጋር እንዴት ልንደመር ነው?
ለማንኛውም የአባቶቻችን አምላክ የተመሰገነ ይሁን፡፡
እስካንም የመጣነው እነርሱ በጣሉልን የአንድነት እርሾ እንጅ በእኛ አብሮ የመኖር ልምድ ነው ብየ አላምንም፡፡ እነርሱ አይደለምና ኢትዮጵያን አፍሪካን አንድ የሚያደርግ እርሾ ጥለው በማለፋቸው ነው እስካሁን ያለነው፡፡ ይህንን አለማድነቅ አለማወቅ ብቻ ነው የሚሆነው፡፡

Facebook Comments

Post Author: መላኩ አላምረው

መላኩ አላምረው
Melaku Alamrew