Dr Abiy Ahmed

ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የሚመራው የልኡካን ቡድን በአሜሪካ ዋሽንግተን ለሚያደርገው ጉብኝትና ህዝባዊ ጉባኤ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት

በኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የሚመራው የልኡካን ቡድን በአሜሪካ ዋሽንግተን ለሚያደርገው ጉብኝትና ህዝባዊ ጉባኤ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለጸ፡፡

የዋሽንግተን አዘጋጅ ኮሚቴ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የተለያዩ አካላትን በማስተባበር በህዝባዊ ውይይቱ ላይ ለመሳተፍ የሚመጡትን እንግዶችን በአግባቡ ለማስተናገድ ኮሚቴው በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር በመሆን በቂ ዝግጅት ተደርጓል፡፡

በዋሽንግተን የኢትዮጵያዊያን የታክሲ ባለቤቶችን፤ በርካታ በጎ ፍቃድ አገልግሎት ሰጪዎችን፤ የመገናኛ ብዙሃንን በማስተባበር ነው ህዝባዊ ውይይቱን የተሳካ ለማድረግ እየተሰራ ያለው ብለዋል የአስተባባሪ ኮሚቴው የሚዲያ ተጠሪ አቶ አቤል ጋሻዬ፡፡

በዋሽንግተን እንዲህ ዓይነቱ ውይይት መካሄዱ የዲያስፖራውን አንድነትና ትብብርን በማጠናከር ለሃገሪቱ እድገት የበኩላቸውን ድርሻ አንዲወጡ ያደርጋል ብለዋል በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ካሳ ተክለብርሃን፡፡

“የጥላቻና የልዩነት ግንብን አፍርሰን የይቅርታና የፍቅርን ድልድይን እንገንባ” በሚል መርህ ቃል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አይመድ በዋሽንግተን ከኢትዮጵያዊያንና ከትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጋር ህዝባዊ ውይይት ለማካሄድ ሃምሌ 21/2010 ቀነ ቀጠሮ ተይዟል፡፡

ምንጭ – ኢቢሲ

Facebook Comments

Post Author: መላኩ አላምረው

መላኩ አላምረው
Melaku Alamrew