አማራ ክልል እና ጤና (የሺሐሳብ አበራ)

በአማራ ክልል፡- • አንድ ሆስፒታል ለ1.2 ሚሊዮን ህዝብ ያገለግላል፤ ተጨማሪ 210 ሆስፒታሎች ያስፈልጋሉ • አንደኛ በተባለው ክልል ግን አንድ ሆስፒታል ለ46 ሺህ ህዝብ ብቻ ያገለግላል በኩር ሕዳር 24/2011ዓ.ም፦ የጤና ተቋማትና አማራ ክልል በአማራ ክልል የጤና እንቅስቃሴ ዙሪያ የዳሰሳ ጥናት ያደረጉት ዶክተር አንድነት አዱኛው ሰሞኑን የክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ በተሳታፊነት ተገኝተው ነበር […]

የዶክመንታሪ ሚናና “ምናባዊው…”

የዶክመንታሪ ሚናና “ምናባዊው…” (Asemahegn Asires – Journalism Instructor) … “ምናባዊው…” በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ዘጋቢ ዶክመንታሪ (Expository Documentary) በጭብጡ እና ይዘቱ የበዛውን ሕዝብ ከማስደመም አልፎ አሳዝኗል፤ አስለቅሷል፡፡ እንዲህ ያለ ታምር በሆሊውድ ፊልሞች እንኳ አላየንም፡፡ ምን ያለ ዝቅጠት፣ ምን ያለ የቁም ሞት፣ ምን ያለ ብልግና፣ እንዴት ያለ ቀውስ ውስጥ እንደገባን፣ ይመሩናል ብለን ገንዘባችን ላይ እንዲያዝዙ ያስቀመጥናቸው ሰዎች […]

ትህነግ ሰው አይደለም፡፡የሰው ልጅን ባህሪ አይወክልም፡፡ – የሺሀሳብ አበራ

የሰው ልጅ የርህራሄ ወለሉም ሆነ የጭካኔ ጣራው የሚያርፍበት ወሰን አለው፡፡ በዚህ ወሰን መሰረትም ህጎች ይሰራሉ፡፡ … በኢትዮጵያ በትህነግ መሪነት የተሰራው ግፍ ግን ከሰው ልጆች የባህሪ ወሰን ሁሉ ያልፋል፡፡የብልት ቆዳ ከመግፈፍ እባብ እያረቡ ከእባብ ጋር እስከ ማሳደር የደረሰ የህይወት ቅጣት በሰው ልጆች ላይ አድርሳለች፡፡ … የትህነግን ክፉነት የዓለም የወንጀለኞች ማህደር ሁሉ ከወንጀል ሜኖው(ዝርዝር) ውስጥ ይተርፍበታል፡፡ ከባዱ […]

አዲስ አበባ ወይስ ጓንታናሞ…

አዲስ አበባ ወይስ ጓንታናሞ… * ጠላት ሀገር እንኳን በዚህ መልኩ አይዘረፍም! ~ ጠቅላይ አቃቢ ህግ ብርሃኑ ጸጋዬ * አዲስ አበባ ውስጥ 7 ግፍ የሚፈፀምባቸው ድብቅ እስር ቤቶች ተገኙ * የሰኔ 16ቱ የአዲስ አበባው የቦምብ ጥቃት የብሔራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎት የቀድሞ ኃላፊ የተመራ ነው *** « በአዲስ አበባ ዜጎች ከሰባት ወደማያንሱ ስውር ማሰቃያ ስፍራዎች ‘በአምቡላንስ እየተጓጓዙ!’ […]

የሕይወት ምንጭ አለ

መኖርህን ማይወድ… ሸክም ሲያበዛብህ፣ ነፍስህን ሊቀጣ፤ ከሸክምህ የሚልቅ… ጽናት በመላበስ፣ ፈንቅለኸው ውጣ! … . ተስፋ ለማይቆርጥ… ማስተዋል ለቸረው፣ ጥበብ ለታደለ፤ ለቀብሩ ብለው… ከሚጭኑት ሸክም፣ የሕይወት ምንጭ አለ። ዳግም የሚወልድ…. ከሞት የበረታ………… ከኃይላት ያየለ !!! Share this…FacebookemailGoogle+TwitterLinkedin

ተቃርኖ – የሺሀሳብ አበራ

ተቃርኖ – የሺሀሳብ አበራ ለህዳሴው ግድብ አማራ ከ 1.2 ቢሊየን ብር በላይ በማዋጣት ከሃገሪቱ ቀዳሚ ነበር፡፡ነገር ግን ከ 30% ሳያልፍ 64% ደርሷል ተብሎ ብሩ ተዘረፈ፡፡ በህዳሴው ግድብ የሚሰሩ አማራዎችም ይታሰሩ እና ይፈናቀሉም ነበር፡፡ …. የሌለ ለመፍጠር 1.2 ቢሊየን ብር ያዋጣው አማራ ጣናም ሆነ ላሊበላ የነበሩት ሲጠፉ 50 ሚሊየን ገና አላዋጣም፡፡ መቼም ሃገሪቱ ጣና ሆነ ላሊበላ […]

Anti Amhara Spirit

የአማራ-ጠልነት መንፈስ ሲወርድ ሲዋረድ

(መላኩ አላምረው) —› የአማራ-ጠልነት ጠንሳሽ ጥልያን ነች። ‹‹ጣልያን ደግሞ አማራን ለምን ጠላችው›› ብላችሁ እደማትጠይቁኝ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ በ5 ዓመቱ ጦርነት ወቅት ከ95 በመቶ በላይ የኢትዮጵያ አርበኞች በጎጃም፣ በሸዋ፣ በጎንደርና በወሎ ብቻ ይገኙ እንደነበር ማስታወስ በቂ ነውና፡፡ (ፕ/ር መስፍን ከ85 በመቶ በላይ አርበኞች እነ በላይ ዘለቀን መሪ አድርገው ጎጃም ላይ ተጋድሎ እንዳደረጉ ጽፈዋል፡፡) የጣልያን ክፋት አማራ-ጠልነቷ አልነበረም። […]

Eskindir Nega

ፍቅር፣ ፍትሕ እና ሰላም የኢየሱስ መንገድ

በዚህ ልዩ ዕትም፣ ጋዜጠኛና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች የሆነው እስክንድር ነጋ የሕንጸት ዕንግዳ ሆኖ ቀርቧል። አገራችን ኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶችና ዴሞክራሲ የሚከበሩባት አገር እንድትሆን መሥዋዕትነትን የጠየቀ ትግል አድርገዋል ከሚባሉት ግለ ሰቦች መካከል አንዱ እስክንድር ነው። በዚህም፣ ከዘጠኝ ጊዜያት በላይ ደጋግሞ ለእስር የተዳረገው እስክንድር፣ በአጠቃላይ ከዘጠኝ ዓመታት በላይ በእስር አሳልፏል።ጋዜጠኛና አክቲቪስት እስክንድር ነጋ በተለያዩ ጊዜያት፣ ከተለያዩ ተቋማት ሽልማቶች […]

Hachalu Hundesa

ኢትዮጵያ የ80 ቀለማት ውሕድ ሥዕል ናት፤ ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው / ድምጻዊ ሀጫሉ

ሬዲዮ ፋና:- ‹‹ለአንተ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነትን ምንድነው?››ድምፃዊ ሀጫሉ፡- ‹‹ለእኔ ኢትዮጵያ የቀለም ውሕድ ሥዕል ናት። ኢትዮጵያን ስንሥላት 80 ቀለማትን ቀላቅለን ነው የምንሥላት። እነዚያ 80 ቀለማት የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ናቸው። ለእኔ ኢትዮጵያዊነት የ 80 ብሔር ብሔረሰቦች ድምር ውጤት ናት። በኢትዮጵያዊነቴ ማንም ሰው አንተ ‹ኢትዮጵያን አትወድም ወይም ትወዳለህ› ሊለኝ አይችልም። ምክንያቱም ቅድመ አያቴ ‹ቦንሲቱ ቃበታ› ከዚህ መቀሌን ነፃ […]

Abiy Ahmed

ለግለሰቦች ከማጨብጨብ ባሻገር ተቋማትን እንፍጠር – የሺሀሳብ አበራ

ዶክተር አብይ እንደ ቮልት ሩጠው ግባቸውንም በሰበርዜና አፍጥነውት ነበር፡፡ ሰበር ዜናው ከሰሞኑ ርቋል፡፡ዶክተር አብይም በሁለት ሳምንታት ውስጥ እንግዳ ነገር ይዘው አልተከሰቱም፡፡ እንግዳ ነገር ብቻ ሳይሆን እሳቸውም ብዙ እየታዮ አይደለም፡፡ .. ጠሚዶ አብይ ሃገሪቱን ሊያረጋጉ የሚችሉ በርካታ ካርዶችን መዘው ተጫውተዋል፡፡ አሁን የወዲያው የመፍትሄ ካርዶች አልቀዋል፡፡ ሰበር ዜናውም እንደ ኤሊ አዝግሟል፡፡ ያለፉት ሰበር ዜናዎች የጠየመውን የህዝብ ፊት […]