ለልጄ ምን ብዬ ልንገራት? (አንዲት የጂግጂጋ ኗሪ እናት)

ለልጄ ምን ብዬ ልንገራት? (አንዲት የጂግጂጋ ኗሪ እናት) መልስ ባገኝም ባላገኝም የተፈጸመብኝን ግፍ እናገራለሁ፡፡ የእኔ በደል በምን ይካሳል? ቁስሌ በምን ይድናል? የ4 ዓመት ልጄን እንደታቀፍሁ ለ3 ቀናት በቤተ ክርስቲያን ተጠልየ ቆይቼ ዛሬ ቤቴ ገባሁ፡፡ ቤቴ ተዘርፏል፡፡ በባዶ ፍርስራሽ ቤት ኩርምት ብያለሁ፡፡ ልጄ በርሃብ ተዳክማብኝ ነበርና የሶማሌ እናቶች የሚበላ ነገር አምጥተውልኝ አቀመስኋት፡፡ እህል በአፏ እንደዞረ ተነቃቃች፡፡ […]

Mahibere Kidusan

በኢትዮጵያ ሱማሌ ክልል በተከሰተው ችግር ከማኅበረ ቅዱሳን የተሰጠ መግለጫ!

“እንግዲያስ ሰላም የሚቆምበትን እርስ በርሳችንም የምንታነጽበትን እንከተል።” /ሮሜ 14፥19/ በሀገራችን በኢትዮጵያ የሚካሔደውን የመንግሥት የአሠራር ለውጥ ተከትሎ ላለፉት ጥቂት ወራት በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶች መከሰታቸው የሚታወቅ ነው፡፡ በግጭቶችም ከሀብት ውድመት እስከ ክቡሩ የሰው ሕይወት ኅልፈት ድረስ መከሰቱ እና በዚህም መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ማዘኑና ለመፍትሔውም በሚችለው ሁሉ መረባረቡ የሚታወቅ ነው፡፡ ባለፉት ሁለት ቀናት በሶማሌ ክልል የተከሰተው ግን በተለይ […]

Ethio-Somale

አሳዛኝም፣ አናዳጅም፣ ዘግናኝም፣ አከራካሪ ዜና/መረጃዎች፡-

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በኢትዮ-ሶማሊ እየተካሄደ ያለውን የቤተ ክርስቲያን ማቃጠልና የሰው ግድያ በጽኑ እንደምታወግዝ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ገልጹ፡፡ ድርጊቱ በአስቸኳይ እንዲቆምም አሳስበዋል፡፡ -› የኢትዮ-ሶማሌ ተወላጆች ናቸው የተባሉ በርካታ ሰዎች አዲስ አበባ በመከላከያ ሚኒስትር ቢሮ/አምባሳደር አካባቢ ‹በሰልፍ› ተገኝተው በጂግጂጋ እየተካሄደ ያለውን ሁከትና ሥርዓት አልበኝነት መንግሥት ጣልቃ ገብቶ እንዲያስቆምና አብዲ ኢሌን ከሥልጣን እንዲያወርድ ጠይቀዋል፡፡ ‹‹ፍትሕ […]

ፓትርያርክና ፕትርክና / ዲ/ን ዳንኤል ክብረት

ከሰባት ዓመታት በፊት ነበር፤ ለብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ቃለ መጠይቅ ማድረግ በመንበረ ፓትርያርክ ግቢ በሚገኘው ቢሯቸው ወደ አሥር ሰዓት አካባቢ ከሌሎች ባልደረቦቼ ጋር ተገኝቼ ነበር፡፡ ያ ቃለ መጠይቅ ወደ አራት ሰዓታት ያህል የፈጀና በሐመር መጽሔት ላይ በተከታታይ የወጣ ነበር፡፡ በመካከል ላይ ቤተ ክርስቲያኒቱ በወቅቱ የነበረችበትን ሁኔታ የሚያነሣ አንድ ጥያቄ ተሰነዘረላቸው፡፡ መጀመርያ በመዳፋቸው አገጫቸውን ያዙና ወደ […]

ክቡር ዶክተር ዐቢይ “ተደመሩ” ስትለን እንዳንታዘዝ፥ የኢሕአዴግ ሕገ መንግሥት (በየክልላችን አስሮ) ይከለክለናል›› / ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ

‹‹“ያለፈውን በይቅርታ እንለፈው”›› አልከን እንጂ፥ የኢትዮጵያ ሕዝብ ባለፉት 50 ዓመታት የደረሰበት ሥቃይ በ5ቱ ዓመት የፋሺስት ወረራ ዘመን ከደረሰበትሥቃይ በዓይነትም በብዛትም የላቀ ነው። የየካቲት 12ን ጭፍጨፋ ትተን፥ በፋሺስት ዘመን የኢትዮጵያውያን ዓሥር ጥፍሮች አንድ ባንድ አልተነቀሉም። እንደ ቅዱስ ጴጥሮስ ቁልቁሊት ተሰቅለው አልተገረፉም። ጣልያኖች በወንድ ብልት ላይ ውሀ የሞላበት ጠርሙስ አላንጠለጠሉበትም። አካለ ጎደሎ የሚያደርግ ቅጣት አልቀጡም። ከፋሺስቶቹ ጋር […]

mekelle airport

መቀሌ ያረፉት 40ዎቹ ታጣቂዎች ማንነት ታወቀ፡፡

እሑድ ሐምሌ 22 ቀን 2010 ዓ.ም. በኢትዮጵያ አየር ኃይል አውሮፕላን መቀሌ አሉላ አባነጋ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት እንደደረሱ በቁጥጥር ሥር የዋሉት 40 ታጣቂዎች፣ የፌዴራል ፖሊስ የኤርፖርት ጥበቃ አባላት ናቸው፡፡ ሪፖርተር ‹‹ታማን ምንጮቹን›› ጠቅሶ እንደዘገበው የኤርፖርት ጥበቃ አባላት የታጠቁ ስለሆኑ በሲቪል አውሮፕላን ሊጓጓዙ ስለማይችሉ… በኢትዮጵያ አየር ኃይል አንቶኖቭ አውሮፕላን ቅዳሜ ዕለት ከደብረ ዘይት አየር ኃይል በመነሳት ቦሌ […]

ለኢትዮጵያ ያላቸውን የጥላቻ ጥግ ለማሳየት የሀገር ጀግናነት ኒሻን ሊሸለም የሚገባውን ገደሉት።

ለኢትዮጵያ ያላቸውን የጥላቻ ጥግ ለማሳየት የሀገር ጀግናነት ኒሻን ሊሸለም የሚገባውን ገደሉት። — ኢንጅነሩን ለመጀመሪያ ጊዜ በዓይኔ ያየኋቸው በ2004 ዓ.ም ነው፡፡ ከተለያዩ ሚዲያዎች ጋር ለ4 ጊዜ ያህል ሄጃለሁ፡፡ 4 ጊዜም አግኝቸዋለሁ፡፡ እዛው የሕዳሴው ግድብ ከሚገነባበት ጉባ፡፡ ኢንጅነር ስመኘው በቀለን ለማየት የነበረኝ ጉጉት የሕዳውን ግድብ ከማየት አይተናነስም ነበር፡፡ ልክ እንደደረስን በፈገግታ ‹‹እንኳን ወደዚህ የሁሉም ትዮጵያውያን የላብ ጠብታ […]

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ስመኘው በቀለ መስቀል አደባባይ መኪናቸው ውስጥ ሞተው ተገኝተዋል።

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ስመኘው በቀለ መስቀል አደባባይ መኪናቸው ውስጥ ሞተው ተገኝተዋል። ያልታደለች ሀገር… ዕንቁ ኢንጅነሯን አጣች፡፡ የገዳዮች ማንነትና ከገዳዮች ጀርባ ማን እንዳለ ባይረጋገጥም…. በሰው እጅ እንደተገደሉ ግን ታውቋል፡፡ የሸሚዝ ኮሌታቸው ተቀዶ በግራ ጆሯቸው እየደሙ እንዳዩአቸው እማኞች ተናግረዋል። ከሕሴው ግድብ ጋር የተያያዘ ብዙ ምሥጢር ስለያዘ ግድያው ከዚህ ጋር የተያያዘ እንደሚሆን ይገመታል፡፡ […]

Yohannes Mekonen

ከምር ግን ሀገሪቱ የማን ናት? የዜጎች ወይስ የቡድኖች? / መ/ር ኢ/ር ዮሐንስ መኮንን

እንኳንስ በአንድ ሀገር በአንድ ቤተሰብ ውስጥም የሚኖሩ አባላት የተለያየ ፍላጎት እና አመለካከት ቢኖራቸው የሚጠበቅ እና ተፈጥሮአዊ ነው። ነገር ግን ”እኔ እንደማምነው እመን። እኔ እንደምመርጠው ምረጥ” ብሎ አንደኛው ሌላኛውን መብት እና ፍላጎት በማስጨነቅ እና በማስገደድ የጫነበት እንደሆነ ወንጀልም አደጋም ይሆናል። እኔ በግሌ በዜግነት እና በግለሰብ ነጻነት (ሰው በመሆን) ላይ የተመሠረተ ፍልስፍናን የምትከተል ሀገር እንድትኖረኝ የምመኘውን ያህል […]

Church and Mosque in Ethiopia

ሙስሊም ነኝ – በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እኮራለሁ / ኢብራሂም ሙሉሸዋ

ቆይ አሁን «አንተ ሙስሊም ሆነህ ስለ ኦርቶዶክስ ምን ገደደህ?» ብባል ምን እላለሁ? ጉድ አኮ ነው! የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን የኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያነት ማሳያ ትልቅ የአገር ሀብት ናት። ቤተ ክርስትያኒቱ ከመንግስት ጋር ከነበራት ግንኙነት ጋር በተያያዘ የተፈጠሩ ችግሮች መኖራቸው አሌ ባይባልም በሌላው ጎን ግን ቤተ ክርስትያኒቱ ለአገራችን ፓለቲካ፣ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እድገት ያደረገችው አስተዋፅኦ በምንም […]