Addis Ababa

አዲስ አበባ፣ ከየት ወደየት? (ዶ/ር ሺመልስ ቦንሣ)

“የድሮዋ በረራ (የአሁኗ አዲስ አበባ) የአምሃራ፤ ጉራጌ እና ጋፋት ክርስትና ተከታዮች ይኖሩባት የነበረች ከተማ ነች” በመጀመሪያ የዛሬ አንድ መቶ ሠላሳ አንድ አመት እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1878 ንጉሰነገስት ምንሊክ ወደ አርሲ ሰራዊታቸውን ይዘው ይዘምታሉ። ባልተቤታቸው እቴጌ ጣይቱ ደግሞ እንጦጦ የነበረውን የመንግስት መቀመጫ ወደ አሁኗ አዲስ አበባ ያዛውራሉ። ለጤና ተመራጭ የሆነው ፍልውሃ ፊንፊን ይልበት የነበረው ቦታ ለከተማው […]

Ethiopian Flag

አረንጓዴ-ቢጫ-ቀይ ሰንደቅ ዓላማችንና ባንዲራቸው!

(መላኩ አላምረው) … ከኢትዮጵያም አልፎ የአፍሪካ ሀገራትን ‹‹የአረንጓዴ-ቢጫ-ቀይ››ን የሰንደቅ ዓላማ ቀለማት አመራረጥና ታሪካዊ አመጣጥ ስንዳስስ…. በሀገራችን ታሪካዊትነትና የነፃነት ዓርማነት ኩራት ይሰማናል፡፡ እነዚህ የእኛ ሰንደቅ ዓላማ ቀለማት (አረንጓዴ-ቢጫ-ቀይ) ‹‹የፓንአፍሪካኒዝም ቀለማት›› ተብለው እንደሚጠሩ እናውቅ ይሆን? በሉ ከዛሬ ጀምሮ እንወቅ፡፡ እነዚህ ሦስቱ ቀለማት ‹‹የፓንአፍሪካኒዝም ቀለማት›› የመባላቸውም ሆነ ለአፍሪካ ሀገራት ሁሉ የነፃነት ምልክት ሆነው የመታየታቸው ምሥጢር ደግሞ ‹‹ኢትዮጵያ›› ናት፡፡ […]

General Atinafu

መንግሥቱ እና የኮሎኔል አጥናፉ ኑዛዜ / ቢቢሲ አማርኛ

ኮ/ል መንግሥቱ ደርግን ኮትኩተው አሳድገውት ይሆናል። ነገር ግን አልወለዱትም። የደርግ እናትም አባትም ኮ/ል አጥናፉ ናቸው። ኾኖም ደርግ ፈጣሪውን መልሶ ለመብላት የወሰደበት ጊዜ ከ5 ዓመት ያነሰ ነበር፡፡ ኅዳር 3/ 1970 በዕለተ ቅዳሜ አጥናፉ ተገደሉ። “አብዮት ልጆቿን በላች” ተባለ። ሲያልቅ አያምር ሆኖ እንጂ መንጌና አጥናፉ ጎረቤት ነበሩ። ሚስቶቻቸው ውባንቺና አስናቀች በአንድ ስኒ ቡና ጠጥተዋል። ትምህርትና ትዕግስት ከነሱራፌል […]

ኢትዮጵያ የሚለው ስያሜ ከየት ተገኘ?

“ኢትዮጵያዊነት” ከሚለው ቃል ጋር፡ የጥሬ ዘርና የምሥጢር፥ የዘይቤና የትርጉም ተዛምዶ ያላቸው፡ በዓለም ሕዝቦችና ቋንቋዎች ዘንድ የታወቁ፡ አንዳንድ ይፋ ቃላት አሉ። ከእነዚህ መካከል የሚከተሉት ተጠቅሰዋል፦ ፩ኛ. “ኢትዮጵያ” ለማለት፡ “ጦብያ” የሚለው ትውፊታዊ፥ ምጽሓፋዊና ሕዝባዊ ቃል፤ ፪ኛ. ጥንታውያን የዓለም ፈላስፎችና ደራስያን፡ የኢትዮጵያን፡ ምድራዊት ገነትነትና የኢትዮጵያውያንን መልአካዊ አኗኗር፡ በመንፈስ በማየትና በዜና በመስማት፡ የኢትዮጵያን፡ ማንነትና የኢትዮጵያዊነትን ምንነት፡ በየጽሑፋቸው ለመግለጽ ይጠቀሙበት […]

የፕሮፌሰር አስራት ደግነት፣ ትህትና እና ፈዋሽነት ጥቂት ማሳያዎች!

1) አንድ ጊዜ ከአርባ ምንጭ የመጡ አንድ ታካሚ፣ “አስራት የሚባል ፀበል ፈልቋል ስለተባልሁ ነው ወደዚህ የመጣሁት” ያሉኝን አስታውሳለሁ። ፕሮፌሰር አስራት በሽተኞችን ኦፕራሲዮን ከማድረጋቸው በፊት የመጀመሪያውን ስራ ለእግዚአብሄር ይሰጣሉ። ፀሎት ሳያደርጉ ስራቸውን አይጀምሩም። 2) 18 አመት እድሜ ያለው አንድ ግሪካዊ ኢትዮጵያ ናዝሬት ለሽርሽር መጥቶ በጥይት ይመታል። አስራት ለወጣቱ ህክምና ካደረገለት በኋላ ወደውጭ ሀገር ሄዶ ስለነበር የግሪክ […]

የእቴጌ ጣይቱና የዳግማዊ ምኒሊክ ባንክን/ኢኮኖሚን “ከቅኝ ግዛት” ነፃ የማድረግ ታሪክ

አንድ ቀን ምሽት የሴት አንበሳዋ እቴጌ ጣይቱ የቁጣ ፊቷን በምኒልክ ዙፋን ፊት አነደደችው። ‹‹ተደፍረናል…! ተንቀና…! በገዛ ሀገራችን የራሳችን ዜጎች በእንግሊዞች እየታሰሩ መሆኑን ሰምተህልኛል?››… ‹‹ምን አልሽኝ ጣይቱ? መታሰር አልሽኝ?›› ንጉሠ ነገሥቱ የሰማውን ማመን አቅቶት ጥያቄዋን በጥያቄ መለሰ። ‹‹አዎ መታሰር! እንግሊዞች ዜጎቻችንን በሐበሻ ባንክ ዕዳ እያሰሩ ነው። ይህ ትልቅ ድፍረትና ንቀት ነው። ለዚህ ዋጋ ይከፍሉበታል!›› …እትጌ የበለጠ […]

ሰላዩ ባሻ አዋሎም (ባሻይ ኣውዓሎም) – ለአድዋ ድል ትልቅ ድርሻ የተወጡ ኢትዮጵያዊ ጀግና !

እንካ የሀገር ጀግና – እንካ ባለውለታ ተኩሶ ብቻ ሳይሆን – ሰልሎ ጠላት ሚመታ ! . የአድዋ ድል ሲነሳ የባሻ አዋሎምን ድርሻ አለማስታወስ ትልቅ ስህተት ነው፡፡ እኚህ ጀግና በስለላ የተጫወቱት ሚና አንድ ጀግና አርበኛ ተኩሶ በመግደል ካደረገው ድርሻ ከፍ ቢል እንጅ አያንስም፡፡ ‹‹ለመሆኑ ምን ሠርተው ነው?›› አልህ? ተከተለኝ…… በል በስማቸው የታተመውን መጽሐፍ ፈልግና አንብብ – ምን […]