Nile Fall Tis Isat

ወንዙ ጉዞውን ይቀጥላል፤ ምንጮችም የገባርነት ግዴታቸውን ይወጣሉ።

ወንዙ ጉዞውን ይቀጥላል። ምንጮችም ገባርነታቸውን አምነው ለወንዙ ውኃን ያዋጣሉ። ወንዝነት እንደ ዓባይ ነው። ዓባይ ስሙንም ክብሩንም ሞገሱንም እንደያዘ ይጓዛል። ምንጮች ወደ ዓባይ የመደመር ዕድል ብቻ ነው ያላቸው። ሲደመሩ የዓባይን መጠን ያገዝፉታል። ግርማ ሞገስ ይጨምሩለታል። የምንጮች ወደዋናው ወንዝ ወደ ዓባይ የመደመርና የመገበር ጉዳይ የተፈጥሯዊ ግዴታ እንጅ ውዴታ አይደለም። ስማቸውም ክብራቸው ዓባይ ነው። ዋና መታወቂያ ምልክታቸው ነውና። […]

የአዲስ አበባው ‹‹ድጋፍ ለዐቢይ›› ሰልፍ ቅድመ ትንበያ

(መላኩ አላምረው) —› መስቀል አደባባይ የሚኖራት ድባብ በአጭሩ፡- – መስቀል አደባባይ በሕዝብም በማስታወቂያም ትጥለቀለቃለች፡፡ ምን አልባት ከባድ ዝናብ ከጣለ አደባባዩ ብቻ ሳይሆን መላው የአዲስ አበባ ጎዳናዎች በጎርፍ ይጥለቀለቃሉ 🙂 ትልልቅ ባነር የተሸከሙ የሸነግ አባላትም በላብ ይጥለቀለቃሉ 🙁 (ኧረ ቀይ ባሕር ወስዶ ያጥልቅህ… የሚል የእርግማን ድምጽ ተሰማኝ፡፡ አርጎት ነው 🙂 ምነው ቀይ ባሕር በተለይም በአሰብ በኩል […]

Asab Port

‹‹ አይገርምም ?!? ›› (መላኩ አላምረው)

—› ‹‹ገረመው›› የምለው ሁሉም ነገር የሚገርመው ጓደኛ አለኝ፡፡ እርሱ የማይገረምበትን ነገር ፈልጎ ከማግኘት ከጅቦች መሐል ውሻ ወይም ከተኩላዎች መሐል በግ ማግኘት ይቀላል፡፡ በቃ ሁሉም ነገር ይገርመዋል፡፡ የኢትዮጵያ ስም፣ የጣና ውኃነት፣ የመለስ መሞት፣ የአክሱም ሐውልት ከድንጋይ መሆኑ፣ ላሊበላ ከአለት መፈልፈሉ፣ የፍልፍሉ ጥርስ መሸረፍ፣ የኃይሌ ገብረ ሥላሴ መሮጥ፣ የየኃይለማርም ቁመት…. በቃ ሁሉም ይገርመዋል፡፡ ልክ እንዳገኛችሁ ‹‹አይገርምም ግን…›› […]

Hailemariam Desalegn

የቀድሞው ጠ/ሚ ኃይለማርም ደሳለኝ የዶ/ር ዐቢይንን ንግግር በሰሙ ጊዜ

የቀድሞው ጠቅላይ ኃይለማርያም ደሳለኝ የዶ/ር ዐቢይን የፓርላማ ንግግር ከባለቤታቸው ጋር ቁጭ ብለው መነጽራቸውን እየቀያየሩ እየተመለከቱ ነበር። . መሐል ላይ…. “እኔ ‘ምለው ሮማን… ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲህ የመናገር ስልጣን አለው እንዴ?” ብለው ጠየቁ። ደርባባዋ ወ/ሮ ሳቅ ብላ…. “አይ ኃይልዬ… እኔን ትጠይቀኛለህ? ጠቅላይ ሚኒስትር የነበርህ እኮ አንተ ነህ” አለችው። ኃይልሻ አፍሮ አቀረቀረ። ካቀረቀረበት ቀና ያደረገው የጠ/ሚ ዐቢይ “አሸባሪዎች […]

‹‹ግንብ ያስፈልጋልም አያስፈልግምም›› (መላኩ አላምረው)

‹‹ግንብ ያስፈልጋልም አያስፈልግምም›› (መላኩ አላምረው)

በአንዲት ሀገር ትንንሽ ዓሣዎች የሚረብሹት አንድ ባሕር ነበር። የዓሣዎቹ ረብሻ በሐይቁ ዙሪያ የሚኖሩ ሰዎችን ሰላም አልሰጥ አለ፡፡ ትንንሾቹ ዓሣዎች በቡድን በቡድን ሆነው በመንቀሳቀስ ትልቅ ማዕበል ይፈጥሩና ውኃውን እየናጡ ወደ ሰፈር ያስገቡታል፡፡ ከዚያም የሰፈሩ ሰዎች ውኃውን ለማስወገድ ብዙ ይደክማሉ፡፡ ትንሽ ማዕበሉ ጸጥ አለ ብሎ ሰው ለመዝናናት ሲሞክር ዓሣዎቹ በድንገት ንጠው ይልኩታል፡፡ መዝናናቱ ወደ ግርግር ይለወጣል፡፡ እንዲህ […]

(ዝብዘባ) – ኑርዬ አያሌው[ሉሲ]

ወጪ ወራጁን ለመመልከት ያመቸኝ ዘንድ መንገዱ ዳር ባለች አንድ ካፌ ቁጭ ብያለሁ።ጭብጨባዬን ያደመጠች የካፌው ታዛዥ ከተፍ አለች። “ምን ልታዘዝ..?” አለች ቀጠለችና ለስለስ ባለ አንጀት ጎትት ድምፅ ተጎናብሳ…ተቅለስልሳ። ማኪያቶ እንድታመጣልኝ ቀጭን ትዕዛዝ ሰጠኹዋት። … ግን..! እንደ’ኔ ላለ ሰው ከአስተናጋጅ በቀር ሌላ ከትህትና ጋር በአክብሮት ሊታዘዘው የሚችል አንድም ሰው ይኖራል ብዬ አላስብም።ምክንያቱም የለም..! ።ሌላው ቢቀር ታላቅ እና […]

writing Letter

የሦስቱ ደብዳቤዎች አዙሪት / ዲ/ን ዳንኤል ክብረት

“ጨለማውን ደጋግመህ ስላወገዝከው መብራቱ አይበራልህም” የአንድ ትልቅ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበረ ሰው ከደርጅቱ ሲለቅ ለተተኪው ሰው ሦስት ደብዳቤዎችን በሦስት ፖስታዎች አሽጎ በላያቸውም ላይ 1፣ 2 ና 3 ቁጥር ጽፎ ሰጠው፡፡ ተተኪውም ‹ምን ላድርጋቸው?› ሲል ጠየቀው፡፡ ‹ድርጅቱን በምታስተዳድርበት ጊዜ ችግር በገጠመህ ቁጥር በየተራ ከፍተህ አንብባቸው› አለና መለሰለት፡፡ ርክክቡም በዚህ ተጠናቀቀ፡፡ አዲሱ ሥራ አስፈጻሚ ሥልጣኑን እንደተረከበ […]

ሕይወት የልምምድ ውጤት ናት!

… “የእኔ ማር” ስላት የማልወዳት ይመስለኛል። የወደድኋትን ልጅ፣ የእኔዋን ውብ… በቁልምጫ ለመጥራት ብዙ ቃላትን እጠቀማለሁ። እርሷ “የእኔ ማር” የሚለው የቁልምጫ መጠሪያ ከማርም በላይ እንደሚጣፍጣት ትነግረኛለች። ምክንያቱም እርሷ ማር ትወዳለች። በዚያ ላይ ዘመኑ የማሬ ማሬ… ነው። በዚህ ሰሞን የሚወዳትን ሴት ‘የ’ኔ ማር’ የማይል ወንድ ዘመኑን አልዋጀም ማለት ነው። እናም አንድም ዘመኑን የምዋጅ ዘመንኛ መሆኔን ለማሳየት፣ አንድም […]

Dr Abiy Ahmed

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ወንበሮች / ዲ/ን ዳንኤል ክብረት

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በጠዋት ወደ ቢሯቸው ማልደው ሲገቡ የእንግዳ መቀበያ ክፍሉ ወንበሮች ተሰልፈው ጠበቋቸው፡፡ ነገሩ እንግዳ ነው ሆነባቸው፡፡ የዚህን ቤተ መንግሥት ባሕል ገና አልለመዱትም፡፡ የተለመዱ ችግሮችን ባልተለመደ መንገድ እፈታለሁ ብለው ለተነሡት ጠቅላይ ሚኒስትር ነገሩ ከተለመደውም የወጣ መሰላቸው፡፡ ‹ምንድን ነው?› አሉ ሳቅ ይዟቸው፡፡ ‹አሰናብቱን› አለ ደንዳሳ ትከሻ ያለው የቆዳ ወንበር፡፡በታሪኩ ለመንግሥት ቅርብ የሆኑ እንግዶችን በማስተናገድ ይታወቃል፡፡ […]

Bewketu seyum

ዱካውን ማደን – በዕውቀቱ ስዩም

በዶክተር አብይ አህመድ እና በግብረ አበሮቹ መሪነት እየተነቃቃ ያለው የርቅ እና የሆደሰፊነት ባህል አስደናቂ ነው:: በታሪክ ብርቅ ከሆኑ ክስተቶች አንዱን ያስታውሰኛል:: በየጁ የምስፍና ዘመን ደጃዝማች ውቤ የተባሉ መስፍን የራስ አሊን መንግስት ለመቀማት ፈለጉ:: በግብጡ ጎረምሳ አቡነ ሰላማ አይዞህ ባይነት በራስ አሊ ላይ ዘመቱ:: ደብረታቦር ላይ ቅልጥ ያለ ጦርነት ተደርጎ ውቤ እና አቡነ ሰላማ ተሸንፈው ተማረኩ:: […]