mekelle airport

መቀሌ ያረፉት 40ዎቹ ታጣቂዎች ማንነት ታወቀ፡፡

እሑድ ሐምሌ 22 ቀን 2010 ዓ.ም. በኢትዮጵያ አየር ኃይል አውሮፕላን መቀሌ አሉላ አባነጋ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት እንደደረሱ በቁጥጥር ሥር የዋሉት 40 ታጣቂዎች፣ የፌዴራል ፖሊስ የኤርፖርት ጥበቃ አባላት ናቸው፡፡ ሪፖርተር ‹‹ታማን ምንጮቹን›› ጠቅሶ እንደዘገበው የኤርፖርት ጥበቃ አባላት የታጠቁ ስለሆኑ በሲቪል አውሮፕላን ሊጓጓዙ ስለማይችሉ… በኢትዮጵያ አየር ኃይል አንቶኖቭ አውሮፕላን ቅዳሜ ዕለት ከደብረ ዘይት አየር ኃይል በመነሳት ቦሌ […]

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ስመኘው በቀለ መስቀል አደባባይ መኪናቸው ውስጥ ሞተው ተገኝተዋል።

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ስመኘው በቀለ መስቀል አደባባይ መኪናቸው ውስጥ ሞተው ተገኝተዋል። ያልታደለች ሀገር… ዕንቁ ኢንጅነሯን አጣች፡፡ የገዳዮች ማንነትና ከገዳዮች ጀርባ ማን እንዳለ ባይረጋገጥም…. በሰው እጅ እንደተገደሉ ግን ታውቋል፡፡ የሸሚዝ ኮሌታቸው ተቀዶ በግራ ጆሯቸው እየደሙ እንዳዩአቸው እማኞች ተናግረዋል። ከሕሴው ግድብ ጋር የተያያዘ ብዙ ምሥጢር ስለያዘ ግድያው ከዚህ ጋር የተያያዘ እንደሚሆን ይገመታል፡፡ […]

Fire at Prison of Debre markos

ልክ በአሁኑ ሰዓት የደብረ ማርቆስ ማረሚያ ቤት በእሳት እየተቃጠለ ነው፡፡

ልክ በአሁኑ ሰዓት የደብረ ማርቆስ ማረሚያ ቤት በእሳት እየተቃጠለ ነው፡፡ የእሳቱ መነሻ ምን እንደሆነ አልታወቀም፡፡ ፖሊስ እጅግ ዘግይቶ ነው ደረሰው፡፡ የጥይትና የጩኸት ድምጽ እየተሰማ ነው፡፡ በዚህ እስር ቤት ወደ 1600 እስረኞች እንደታሰሩበት ይታወቃል፡፡ እየነደደ ያለው ይኸው ማረሚያ ቤት እየነደደ ነው። መረጃውን እዛው ያለው ‹‹ማረው አበበ›› የተባለ የዩኒቨርሲቲ መምህር ነው በስልክ የነገረኝ፡፡ የበለጠ ለማጣራት ወደ ውስጥ […]

በቦምብ ፍንዳታው ተጠርጥረው የታሰሩ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመብን ነው አሉ

(ሪፖርተር : ታምሩ ጽጌ) ለሦስተኛ ጊዜ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተፈቀደባቸው ለጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) የድጋፍና የምሥጋና ሥነ ሥርዓት ሲከናወን በመስቀል አደባባይ ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም. ተወርውሮ በፈነዳው ቦምብ ምክንያት በእስር ላይ የሚገኙ ተጠርጣሪዎች፣ ሰብዓዊ መብታቸው መጣሱን ለፍርድ ቤት ተናገሩ፡፡ ለሦስተኛ ጊዜ በፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት ዓርብ ሐምሌ […]

No Gun

ከ500መቶ በላይ ሽጉጦች፣ 3 መትረየስ ፣ 100ሺ የሚጠጉ የተለያዩ ጥይቶች እና ከ30 በላይ ክላሽ ተይዟል

በህገ ወጥ የገንዘብና የጦር መሳሪያ ዝውውሩ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር የዋሉት ተጠርጣሪዎች ብዛት 18 ደረሰ። ከአምስት መቶ በላይ ሽጉጦች፣ ሶስት መትረየስ ፣ መቶሺ የሚጠጉ የተለያዩ ጥይቶች እና ከ30 በላይ ክላሽ ተይዟል ሰሞኑን በብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ በፌደራል ፖሊስ እና በኦሮሚያ ፖሊስ ትብብር የተያዙ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች መያዛቸውን ተከትሎዝውውሩ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር የዋሉት ተጠርጣሪዎች ብዛት […]

dANIEL kIBRET

ሙሐዘ ጥበባት ዲ/ን ዳንኤል ክብረት የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቦርድ አባል ሆኖ ተመደበ፡፡

ሙሐዘ ጥበባት ዲ/ን ዳንኤል ክብረት የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቦርድ አባል ሆኖ ተመደበ፡፡ ባለፈው የብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት ኤጀንሲ ዳይሬክተር ሊሆኑ ነው ተብሎ የነበረውየተሳሳተ መረጃ መሆኑ ከታወቀ በኋላ አሁን በተረጋገጠ መረጃ የፕሬስ ድርጅ የቦርድ አባል ሆኗል – የወግ ጸሐፊው ዲ/ን ዳንኤል፡፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባው ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት 8 አባላት ያሉት […]

Eskindir Nega and Abetir Worku

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ አበጥር ወርቁን ጎብኘው

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ አበጥር ወርቁን ጎብኘው ከሁለት ወራት በፊት በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሰቃቂ ጥቃት የተፈፀመበትን ታዳጊ አበጥር ወርቁን ጋዜጠኛና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች እስክንድር ነጋ ጎብኝቶታል፡፡ እስክንድር ከአሜሪካ እንደተመለሰ ይህንን በማንነቱ አሰቃቂ ግፍ የተፈጽመበትን የ14 ዓመት ልጅ አበጥርን ጎብኝቶታል፡፡ አበጥር ወርቁ ለህክምና ወደህንድ አገር ተጉዞ የነበረ ቢሆንም አስፈላጊ ህክምናዎችን ስላልጨረሰ ቀጠሮ ተሰጥቶት ተመልሷል። ‹‹የማይሰበረው ብርቱ ሰው›› […]

Commercial Bank of Ethiopa

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የባንኩን አመራሮች አስጠነቀቁ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የባንኩን አመራሮች አስጠነቀቁ (ታምሩ ጽጌ) ‹‹የተጠየቀው የደመወዝ ጥያቄ ለሚመለከተው አካል ቀርቦ ምላሽ እየተጠበቀ ነው›› (የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሁለት ዓመታት በላይ ያስጠናው አዲስ መዋቅር ሲጠናቀቅ፣ ሠራተኞችና የባንኩ አመራር የተሰማሙባቸው ነጥቦች ሳይካተቱ በመቅረታቸው፣ የሠራተኛ ማኅበሩ ሠራተኞችን ወክሎ አመራሩን አስጠነቀቀ፡፡ ከሁለት ዓመት በፊት አዲስ መዋቅር ለማሠራት የወጣውን የንግድ ባንክ ዓለም አቀፍ […]

Tilaye Gete (PhD)

የትምህርት ዘርፉ በሁለት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ሊመራ ነው / ዶ/ር ጥላዬ ጌቴ

የትምህርት ዘርፉ በሁለት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ሊመራ ነው / ዶ/ር ጥላዬ ጌቴ ባህርዳር፡ሰኔ 28/2010 ዓ/ም(አብመድ)የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ጥላዬ ጌቴ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የትምህርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እንደተናገሩት በአሁኑ ወቅት ያለው የትምህርት ሚኒስቴር አደረጃጀት የአገሪቱ የትምህርትና ስልጠና ለደረሰበት ደረጃ ምላሽ ሰጪ አይደለም። በአገሪቷ የትምህርት ተቋማት እየተስፋፉ በመምጣታቸው፣ ከትምህርት ዘርፉ ውስብስብነት፣ የትምህርት ስርዓቱ ከሚመራበትና በዝግጅት ላይ […]

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የማረሚያ ቤት አመራሮችን ከሃላፊነት አነሳ

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የማረሚያ ቤት አመራሮችን ከሃላፊነት አነሳ አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 27 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የማረሚያ ቤት አመራሮችን ከሃላፊነት በማንሳት አዳዲስ አመራሮች መሾማቸውን ገለፀ። የማረሚያ ቤት አስተዳደር ህገ መንግስታዊ ግዴታውን በተገቢው ሁኔታ መወጣት ባለመቻሉ እና ሰብዓዊ መብቶችን ከማክበር አንጻር ሰፊ ክፍተት በመኖሩ ለውጥ መደረጉን የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ […]