የሕይወት ምንጭ አለ

መኖርህን ማይወድ… ሸክም ሲያበዛብህ፣ ነፍስህን ሊቀጣ፤ ከሸክምህ የሚልቅ… ጽናት በመላበስ፣ ፈንቅለኸው ውጣ! … . ተስፋ ለማይቆርጥ… ማስተዋል ለቸረው፣ ጥበብ ለታደለ፤ ለቀብሩ ብለው… ከሚጭኑት ሸክም፣ የሕይወት ምንጭ አለ። ዳግም የሚወልድ…. ከሞት የበረታ………… ከኃይላት ያየለ !!! Share this…FacebookemailGoogle+TwitterLinkedin

በሐዋሳ የተነሣውን ግጭት ሸሽተው ቤተ ክርስቲያን የተጠለሉ ወገኖቻችንን የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል አጽናኑ።

…. ግፉዓንን አስጠልላ – በቅዱስ ቃሉ ‘ምታጽናና፤ ሐዋርያት የገነቧት – የክርስቶስ ቤት ይህቻትና። . ከተገፉት ጎን የሚቆም – ሐዋርያትን የመሰለ፤ ያዘኑትን የሚያረጋጋ – አባትም ከመቅደሱ አለ። . ይህች ናት ቤተ ክርስቲያን – ይኸው ነው ወጉ የአባት፤ በምድር የሚገፉትን – ወደ ሰማይ በር ማስገባት፤ ከቅዱስ ቃሉ መግቦ – የፍቅር ዘይት መቀባት !!! ።።።።።።።። ።።።። ፎቶ፡ በሐዋሳ […]

ሰይጣን ባንች እንዴት አይቅና !?!

ሰይጣን ባንች እንዴት አይቅና !?!

ሰይጣን ባንች እንዴት አይቅና !?! (መላኩ አላምረው) … የሰማይ ብርሃን ፍንጣዊ – የወረደበት ከሰማይ የዚያ ተራራ ምሳሌ – የታቦር ኮረብታሽ ከላይ… . የፍቅር ሐይቅሽ ከስር – የንጉሥ ማሕተም ከመሐልሽ በተፈጥሮ የተቸረሽ – – – በጥበብ የተሳለልሽ… . ኢትዮጵያዊ በአንድነት – ብሔር ከብሔር ተፋቅሮ ሰሜን ከደቡብ ተጋብቶ – ምሥራቅ ከምዕራብ ተማክሮ በልዩ የእምነት መዝሙር – በልዩ […]

በመፋቀራችን፦ ጌታ ቅር አይለውም፤ አላህ አይከፋውም።

በመፋቀራችን፦ ጌታ ቅር አይለውም፤ አላህ አይከፋውም።

በመፋቀራችን፦ ጌታ ቅር አይለውም፤ አላህ አይከፋውም። (መላኩ አላምረው) —***— መግቢያ፦ ከመካ ቀጥለን፣ ከአፍሪካ ቀድመን፤ በክርስቲያን አምባ፣ መስጊዱን አቁመን፤ እስላም ክርስቲያኑ፣ በአንድ ላይ ከትመን፡፡ በዓላችሁ በዓላችን፣ በዓላችን በዓላችሁ፤ ደስታችሁ ደስታችን፣ ደስያችን ደስታችሁ፤ ሆኖ የጠበቀን፣ ከአበው የወረስነው፤ ኢትዮጵያዊነት! – መለያችን ይህ ነው። -*- ሀተታ፦ በእውነት ከሆነ… በእኛ የደስታ ቀን፣ የእናንተ መንዙማ፤ በእናንተም በዓላት… ያሬዳዊ ዜማ፤ (ለአምልኮ ሳይሆን፣ […]

ቆስቋሽና አቆሳቋሽ

‹‹ቆስቋሽና አቆሳቋሽ››

‹‹ይ’ች ሀገር እንደዚህ፣ የምትታመሰው፤ ማነው ማማሻውን፣ የሚቆሰቁሰው?›› ብለህ የጠየቅኸኝ… ተከሳሽ ፈልጌ፣ የጥንት ማመካኛ፤ ‹‹ሰይጣን ነው›› ልበልህ? ያንን መከረኛ? . አትሸወድ ጓዴ… ከመካከላችን፣ ሥጋ የለበሰ፣ ክፉ ሰይጣን አለ፤ በመንፈስ፣ በግብር፣ ያንን የጥንት ጠላት፣ እ ር ሱ ን የመሰለ። ‹‹ይህ ያልኸውስ ማነው?›› ብለህ እየጠየቅህ፣ ልቤን አታድርቀው፤ አቆሳቋሹ ነው፣ ቆስቋሹን የሚያውቀው። . ያው ላ’ቆሳቋሹ፣ ቆስቋሹን ማጋለጥ፣ ቢመርም ባይመርም፤ […]

Love but don't believe

‹‹ባትጠላውም ራቀው››

(መላኩ አላምረው) —› ‹‹እስኪይዙ ቦታ፣ እስኪደላደሉ፤ ይስቋል ለጠላት፣ እንደወዳጅ ሁሉ፡፡›› እንደሚሉት አበው፣ . ‹‹ጥሩ ወዳጅ መስሎ፣ የቀረበህ ያ ሰው፤ ያንተ የሆነውን፣ ወስዶ ከጨረሰው፤ ብዙ ሳትገረም፣ ብዙም ሳትጃጃል፤ በፍጥነት ከእርሱ፣ መራቅህ ይበጃል፡፡ ፈጠን በል እንጅ ጃል…!   ጥርሱን እያሳዬ፣ ያለህን የሚነጥቅ፤ ወዳጅህ አይደለም፣ ጠላት ነው ተጠንቀቅ፡፡   ያለህን ጨርሶ፣ ወዳንተ ሳይመጣ፤ ከሕይወትህ ይራቅ፣ ከሕይወቱ ውጣ፡፡›› . […]

Marriage Ring

‹‹ላገባ ነው››

(መላኩ አላምረው) —› እስከዚህች ዕለት፡- በሁለት ሐሳቦች፣ ነበርሁ ተወጥሬ፤ አንደኛው ምኞቴ፣ ተሰረዘ ዛሬ፡፡ ከዛሬ ጀምሮ፡- የመንፈስ ልዕልና፣ ምንኩስና ቀረ፤ ሐሳቤ ከገዳም፣ ወደ ሴት ቀየረ፡፡ ባክሽ ይቅር በይኝ፡፣ እንጋባ እያልሽኝ፣ ያኔ የማልኩልሽ፤ እመነኩሳለሁ – አላገባም፣ ያልኩሽ፤ ስንፍናዬ ነበር፣ ከጥበብ መራቄ፤ የጋብቻን ምሥጢር፣ አለመጠንቀቄ፡፡ አሁን ግን ስረዳው፣ አንዱ የጽድቅ በር፣ ጋብቻ ነው ቅዱስ፤ መኝታውም ንጹህ፣ ከቶም የማያረክስ፡፡ […]

Gold

‹‹ወርቅነት››

(መላኩ አላምረው) —› መግቢያ፡- ‹‹ወርቅ ነን›› ያላችሁ… አወ ወርቅ ናችሁ፣ አትጠራጠሩ፤ ግን ከወርቅም በላይ፣ ሰው ለመሆን ጣሩ፤ ወይም ከሰዎች ጋር፣ በመስማማት ኑሩ፡፡ —› ሐተታ፡- በ‹‹ዕንቁ ነኝ›› ስሌት፣ ከሰዎች መለየት፣ ክብር አያሰጥም፤ በሰው ልጅ ተፈቅሮ፣ የማይለበስ ወርቅ፣ ከቆረወቆሮ አይበልጥም፡፡ —› መደምደሚያ፡- በሰው ልጆች ምድር – በውበታም ዓለም፤ ወርቅ ከጌጥነት – ከፍም ዝቅም አይልም፡፡ Share this…FacebookemailGoogle+TwitterLinkedin

Ethiopian Died crossing Sea

‹‹ከእነዚህ መካከል›› – (ባሕር ስለበላቸው ኢትዮጵያውያን)

(መላኩ አላምረው) … መሰደድ የሚሉት፣ ወጥቶለት ክፉ ዕጣ፤ ከእናቱ ከአባቱ… ካገሩ እንደወጣ… ሲጓዝ ሲጓዝ ሲጓዝ – ከጥልቅ ባሕር ደርሶ፤ እንዲህ የሚታየው… ደሙ ከውኃው ጋር – በአሸዋ ላይ ፈስሶ… . ካገሩ ሲወጣ፣ ትልቅ ሕልም ነበረው፤ ምን ዋጋ አለው ታዲያ… ክፉ ዕጣ ፈንታው፣ ባሕር ውስጥ ቀበረው፡፡ —› ከእነዚህ መካከል፣ አንዱ እናቱ ታማ፤ በየጤና ጣቢያው… ደጋግማ ታክማ፤ ሕመሟ […]

ከጓድ መንግሥቱ ለዶ/ር ዐቢይ የተጻፈ ደብዳቤ

ከጓድ መንግሥቱ ለዶ/ር ዐቢይ የተጻፈ ደብዳቤ (መላኩ አላምረው) —//— “እኔ ምልህ ዐቢይ… ከእኔ መውጣት ኋላ የታሰረን ሁሉ፤ ይቅር ይቅር እያለህ ትፈታለህ አሉ። . በሲአይኤ ሴራ፣ በተሰራብኝ ሸፍጥ፣ የተሰደድሁ እኔ፤ ላገሬ እንዳልበቃ፣ ሞት የፈረደብኝ፣ ሙትቻ ወያኔ…! . አሁን ባንተ ዘመን፣ አገሬ ካልገባሁ፣ መቼ ልገባ ነው? አይ የልጅ ነገር፣ እረሳኸኝ እንዴ? ዝም አልከኝ ምነው? … ሲያነደኝ የኖረ […]